የቴዲ አፍሮ ወቅታዊ አቋም ታማኝ በየነን አበሳጭቷል

Posted November 10, 2009 by ethiogossip
Categories: News

ቴዲ አፍሮ ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ ባደረጋቸው ነገሮች አሜሪካ የሚገኘው ታማኝ በየነ እና አንዳንድ ኢትዮጵያዊያን ደስተኛ እንዳልሆነ እየተነገረ ነው፡፡ ቴዲ ከተፈታ በኋላ በቀጥታ ወደ አሜሪካ ሄዶ ኑሮውን እዚያ እንደሚያደርግና መንግስትን ክፉኛ እንደሚተች በእነታማኝ ዘንድ ቢጠበቅም ቴዲ በተቃራኒው አዲስ አበባ በመቆየት እጅግ ደማቅ ኮንሰርት በአዲስ አበባ ስቴዲየም አከናውኗል፡፡ በዝግጅቱና በአንዳንድ ቃለ ምልልሶቹ ላይ የሰጣቸው አስተያየቶችም እንደታሰበው መንግስትን የሚተቹ አልሆኑም፡፡ የኮንሰርቱ አብዛኛው ክፍል በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መተላለፉም አሜሪካ በሚገኙት እነ ታማኝ ዘንድ ብስጭትን ፈጥሯል፡፡  

የቀድሞው የመድረክ አስተዋዋቂ ታማኝ በየነ ሰሞኑን ለአንድ የኢትዮጵያ መፅሄት በሰጠው አስተያየት በቴዲ ወቅታዊ ሁኔታ ግራ እንደተጋባና ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ድምፃዊው ለኮንሰርት ሥራ አሜሪካ ሲሄድ ስለ ጉዳዩ ማብራሪያ እንደሚጠይቀው ገልጿል፡፡ በመፅሄቱ ላይ እንደተነበበው ቴዲ የአውሮፓ ኮንሰርቶቹን ሥራ ውል የተፈራረመው የመንግስት ደጋፊ ከሆነ ሰው ጋር ነው ያሉ አንዳንድ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ሰዎች ለዝግጅቱ ቲኬት እንዳይቆርጡ ቅስቀሳ አድርገዋል ተብሏል፡፡ ነገር ግን ቴዲ በፍራንክፈርት ጀርመን ባቀረበው የመጀመሪያ ኮንሰርት ከ1 ሺህ 3 መቶ በላይ ህዝብ ተገኝቶ በደማቅ ሁኔታ መጠናቀቁ ታውቋል፡፡

የድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ አዲስ ስም ‹ተከተል ፎርሲዶ›

Posted November 6, 2009 by ethiogossip
Categories: Gossips

የምን ሚኒስቴር መስራ ቤት ሚኒስትር መሆናቸውን አሁን ባላስታውስም በአንድ ወቅት ‹ተከተል ፎርሲዶ› የሚባሉ ሚኒስትር ነበሩ፡፡ አሁን እሳቸው ከአገራችን ፖለቲካ ደብዝዘዋል ስማቸው ግን እንደ አዲስ በድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ተነስቷል፡፡ ታሪኩ እንዲህ ነው… ድምፃዊት ማንአልሞሽ ዲቦ በከፋ ሁኔታ ታማ ሆስፒታል እንደገባች ከዚህ በፊት አስነብቤአችኋለሁ፡፡ ለድምፃዊቷ ማሳከሚያ የሚሆን ገንዘብም ከተለያዩ አርቲስቶች ገንዘብ እየተሰጣት ነው፡፡

በተለይ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ሆስፒታል ድረስ ሄዶ ጎብኝቶ ብር 20 ሺ ከሰጣት በኋላ የበርካታ አርቲስቶች ትኩረት ስባለች፡፡ ታደለ ሮባ ብር 5 ሺ፣ ታደለ ገመቹ ብር 2 ሺ እንዲሁም ጎሳዬ ተስፋዬ ብር 20 ሺ ሰጥተዋታል፡፡ ጎሳዬ ተስፋዬ ‹ተከተል ፎርሲዶ› የሚለውን አዲስ ስም ያገኘውም ከዚህ በኋላ ነው – ቴዲ አፍሮን ተከትሎ እሱም 20 ሺ ብር ሰጠ በሚል፡፡ እንደዛም ሆኖ ግን ለጎሳዬ ያለኝ አድናቆት ከፍተኛ ነው… ከገቢ አንፃር ከቴዲ ጋር ባይመጣጠንም ቀና ልብ እንዳለው ግን አሳይቷል፡፡


Follow

Get every new post delivered to your Inbox.