ኢትዮጵያ እና የ2032 ዜናዎቿ

 

ኃይሌ ገ/ስላሴ ከጆሃንስበርግ ኦሎምፒክ ያለ ሜዳሊያ የተመለሱት አትሌቶችን ተቸ

 

በባንኮክ ታይላንድ የቬተራን ማራቶን ሩጫውን 2፡15 ላይ በማጠናቀቅ በ1ኛነት የጨረሰው አትሌት ኃይሌ ‹ኦሊምፒክ በእኛ ጊዜ ቀረ› በማለት ማማረሩን የኢቲቪ ስፖርት አዛውንት ጋዜጠኛ ሰለሞን ገብረ እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ ዘግቧል፡፡ ሰለሞን በማያያዝም ‹ወደ ባንኮክ ብላክ ኖሮ ዘገባውን በበለጠ ሁኔታ እዘግበው ነበር› በማለት በምቀኝነት ከጉዞው ያስቀሩት የኢቲቪ ሰራተኞችን ወጋ አድርጓል፡፡

 

 

አርቲስት ጥበቡ ወርቅዬ ፀጉሩን ተቆረጠ

 

የ60 ዓመቱ ጎልማሳ አርቲስት ጥበቡ ወርቅዬ ‹ከእንግዲህ ወጣትነት አብቅቷል› በሚል በርካታ ዓመታት ሲንከባከበው የነበረው ፀጉሩን እንደተቆረጠ ኢዜአ በስፋት ዘግቧል፡፡ ምንም እንኳን ኢዜአ በዚህ መልኩ ቢዘግብም አርቲስት ታደለ ሮባ ግን ዘገባውን በማጣጣል ጥበቡ የተቆረጠው አዲስ የከፈተውን ‹ጥበቡ ወርቅዬ የፀጉር አስተካካይ› ፕሮሞት ለማድረግ እንደሆነ ጠቁሟል፡፡

 

በመላው አገራችን በርካታ ሙዚቃ ቤቶች የከፈተው ጥበቡ ከጠላ ቤት እስከ ፀጉር አስተካካይ በመሳሰሉ የኢንቬስትመንት መስኮች እንደተሰማራ ለረዥም ዘመናት አብሮት የሰራውና በቅርቡ ናይት ክለብ ውስጥ የተቧቀሰው ታምራት ደስታ ገልጧል፡፡     

 

ሃይሌ ገሪማ አዲስ ፊልም ሰራ

 

በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2001 ላይ 14 ዓመታት የፈጀ ‹ጤዛ› የተባለ ፊልም ከሰራ በኋላ ላለፉት 30 ዓመታት ጠፍቶ የቆየው ሃይሌ ገሪማ ‹ረመጥ› የሚባል አዲስ ፊልም ሰርቶ ብቅ ብሏል፡፡

 

አፄ ሃይሌ ስላሴ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ‹ምርት 3000›፣ ደርግ ከስልጣን ከወረደ በኋላ ደግሞ ‹ጤዛ› የሚሉ ፊልሞችን የሰራው ሃይሌ አዲስ ፊልም ለመስራት ለምን 30 ዓመታት እንደቆየ ሲጠየቅ ‹ኢህአዴግ ከስልጣን እስኪወርድ ድረስ› በሚል መልሷል፡፡

 

በሌሎች ፊልሞቹ ፀሃፊ፣ ዳይሬክተር፣ ፕሮዲዩሰርና ኤዲተር በመሆን የሰራው ሃይሌ ገሪማ በዚህ ፊልሙ ላይ ደግሞ በተዋናይነትም ተሳትፏል፡፡

 

ሃይሌ ፊልሙ አዲስ አበባ ውስጥ መታየት ሲጀምር ማኪያቶ በሚጠጡና ዶዶራንት በሚጠቀሙ ወጣቶች ላይ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ የስድብ ናዳ ያዘንባል ተብሎ ስለሚጠበቅ ብዙ ወጣቶች ከማኪያቶ ወደ ጠላ ከዶዶራንት ወደ ሎሚ በመሸጋገር ላይ ናቸው፡፡ በመሆኑም የማኪያቶና የዶዶራንት ዋጋ እየቀነሰ የጠላና የሎሚ ዋጋ ደግሞ እየናረ መሆኑ ታውቋል፡፡

 

 

 

 

የኤርትራ ንጉስ ለህክምና ወደ አዲስ አበባ ገቡ

 

ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በርካታ ኤርትራዊያንን እያሰቃዩ፣ እያሰሩና እየረሸኑ በ97 ዓመታቸው አገራቸውን በቅንነት እየመሩ የሚገኙት የኤርትራው ንጉስ ኢሳያስ አፈወርቂ ለህክምና ወደ አዲስ አበባ መግባታቸው ተገለፀ፡፡

 

በኤርትራ የአስተዳደር ለውጥ ያስፈልጋል የሚል ጥያቄ ከተነሳ በኋላ አስተዳደሩ ላይ ለውጥ ለማምጣት ሲባል ራሳቸውን ከፕሬዚዳንትነት ወደ ንጉስነት የለወጡት ኢሳያስ በአዲስ አበባ የህክምና ቆይታቸው የልብ፣ የጨጓራ፣ የጉበት፣ የጭንቅላት፣ የሳንባ፣ የጥርስ፣ የደም ብዛት፣ የስኳርና የስንፈተ ወሲብ ህክምና እንደሚያደርጉ ታውቋል፡፡

Advertisements
Explore posts in the same categories: Imagine This!

One Comment on “ኢትዮጵያ እና የ2032 ዜናዎቿ”

  1. worldmanb Says:

    oh my God! What an amazing website in Ethiopia!!!!
    Really i loved it more than that you can expect and i would
    like to say keep it up !!!!!!!!!!


Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s


%d bloggers like this: