በቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ሰው ሞተ

ባለፈው እሁድ ጥቅምት 1/2002 ላይ በአዲስ አበባ ስታድየም በተካሄደው የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርት አንድ ሰው ህይወቱ አለፈ፡፡ መግቢያው ብር 10፣ 50፣ 200 እና 300 በነበረው ይህ የቴዲ ኮንሰርት ላይ መግቢያ ብር ወይም ቲኬት አጥቶ መሆኑ ያልተረጋገጠው ሟች ወጣት ህይወቱ ያለፈው ኮንሰርቱን ከስታድየም ውጭ ባለ ዛፍ ላይ ወጥቶ ለመመልከት ሲሞክር በመውደቁ ነው፡፡

በልመና የሚተዳደሩ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ለሚሰራ ምግባረ ሰናይ ድርጅት ገንዘብ ለማሰባሰብ ታቅዶ በተካሄደው በዚህ የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ላይ እስከ 25 ሺ የሚገመት ተመልካች የተገኘ ሲሆን ቴዲ አፍሮ ከምሽቱ አንድ ሰዓት እስከ ምሽት 5 ድረስ አድናቂዎቹን አዝናንቷል፡፡

ቴዲ አፍሮ ለወ/ሮ አበበች ጎበና ድርጅት የ100,000 ብር እርዳታ እንዲሁም ለገጣሚና ደራሲ ይልማ ገ/አብ የወርቅ ብዕር ሸልሟል፡፡

Advertisements
Explore posts in the same categories: News

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s


%d bloggers like this: