መለስ ዜናዊ VS ቀነኒሳ በቀለ

አንዳንድ ሰዎች አትሌት ቀነኒሳን እንዲህ ሲሉ መከሩት…

 ‹አንተ እኮ በሩጫ እና በኢንቨስትመንት ኃይሌ ገ/ስላሴ ላይ እየደረስክበት ነው፡፡ ነገር ግን ኃይሌ በማህበራዊ ኑሮ ላይም በብዙ መንገድ ይሳተፋል፡፡ ሽማግሌ ሆኖ ከመንግስት ጋር በመደራደር የቅንጅት አመራሮችን ከእስር ቤት አስፈትቷል፡፡ አንተ ደግሞ ቴዲ አፍሮን ማስፈታት ትችላለህ›

 – ቀነኒሳ በሁኔታው ተስማምቶ ቴዲ አፍሮን ለማስፈታት ጥረቱን ጀመረ… ወደ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ስልክ ደወለ

 ቀነኒሳ፡ ጤና ይስጥልኝ ክቡር ጠቅላይ ፕሬዚዳንት… ይቅርታ ጠቅላይ ሚኒስትር

 መለስ፡ (ሳቅ) ደህና ችግር የለም… እንዴት ነህ ቀነኒሳ አምበሳ

 ቀነኒሳ፡ ደህና ነኝ

 መለስ፡ ምን እግር ጣለህ

 ቀነኒሳ፡ ምን ስልክ ጣለህ ነው የሚባለው… በእግር አልመጣሁም በስልክ ከቤት ነው…

 መለስ፡ (ሳቅ) ገብቶኛል… ቀነኒሳ… ምን ልርዳህ?

 ቀነኒሳ፡ የቴዲ አፍሮ ጉዳይ ነው ያስደወለኝ

 መለስ፡ ቴዲ አፍሮ ምን ሆነ?

 ቀነኒሳ፡ ከእስር ቤት እንዲፈታ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ነው የደወልኩት…

 መለስ፡ ቀነኒሳ የቴዲ ጉዳይ ፍ/ቤት የያዘው የህግ ጉዳይ ነው

 ቀነኒሳ፡ ዋ! ቴዲ አፍሮ የማትፈቱት ከሆነ ዜግነቴን እቀይራለሁ

 መለስ፡ ቀነኒሳ አገራችንን ያኮራህ ወደፊትም የምታኮራ ጀግና ነህ እንወድሃለን እናከብርሃለን… በዚህ ጉዳይ ከመጣህ ግን አይደለም ዜግነትህ ፆታህን መቀየር ትችላለህ፡፡

Advertisements
Explore posts in the same categories: Jokes!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s


%d bloggers like this: