ድምፃዊ ቴዎድሮስ ታደሰ ቤት ውስጥ ታሰረ

በርካታ ዓመታት ውጭ አገር ቆይቶ ወደ አገሩ በመመለስ ትዳር የመሰረተው ዝነኛውና ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲ ታደሰ በአእምሮ ህመም ቤት ውስጥ መታሰሩ ታወቀ፡፡

አሜሪካ እያለም ያመው እንደነበር የሚነገረው ድምፃዊ ቴድሮስ ታደሰ በሽታው ያገረሸበት የአንጋፋው አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ ልደት በሂልተን ሆቴል በተከበረበት ወቅት መስከረም 17/2002 እንደሆነ የታወቀ ሲዎን ለህመም የዳረገው ነገርም በጥላሁን የልደት ቀን፤ የጥላሁን መታሰቢያ ዝግጅት ሂልተን ውስጥ በተደገሰው ፕሮግራም ላይ ለጥላሁን ክብር ሊዘፈን ቦታው ላይ ተገኝቶ ሲያበቃ እሱ ሊዘፍነው የነበረውን ዘፈን ቴዲ አፍሮ ቀድሞ በመዝፈኑ እንደሆነ የጎሲፕ ምንጮች ጠቅሰዋል፡፡

እንደ ምንጮች መሰረት ታሪኩ እንዲህ ነው፡- ጥላሁን ገሠሠ ሊሰራው ያሰበው ‹ምስጋና› የተሰኘው ዘፈን ጥላሁን ድንገት ሲሞት ለቀብር ስነ ስርዓቱ ድምቀት ሲባል ቴድሮስ ታደሰ፣ ማህሙድ አህመድ፣ ንዋይ ደበበና ፀሐይ ዮሐንስ አንድ ላይ ሆነው እንደዘፈኑት ይታወቃል፡፡ በጥላሁን የልደት ቀን (መስከረም 17/2002) ለአንጋፋው አርቲስት መታሰቢያ በሂልተን ሆቴል ፕሮግራም በተዘጋጀበት ቀን ቴድሮስ ታደሰ ይህንን ‹ምስጋና› የተባለ ዘፈን ለማቅረብ ፕሮግራም ተይዞለት፤ ተሰናድቶ ቦታው እንደደረሰ ድንገት ቴዲ አፍሮ መድረክ ላይ ወጥቶ ይህንን ዘፈን ቀድሞ ሲዘፍንበት ቴዲ ታደሰ በሁኔታው ተበሳጭቶ ከአዳራሹ በመውጣት እዛው አካባቢ ከነበሩ ሰዎች ጋር ተጣልቶ ሄደ፡፡ አዳራሹ ውስጥ የነበሩ ታዳሚዎች እንደሚሉት ቴዲ አፍሮ መድረክ ላይ ወጥቶ ‹ምስጋና› የተባለውን ሲያንጎራጉር የእነ ቴዲ ታደሰን ስም አንስቶ እንኳን ክሬዲት አልሰጠም፡፡ ቴዲ ታደሰ በዚህ ሁኔታ ተበሳጭቶ ከታመመ በኋላ ህመሙ ተባብሶበት በሰንሰለት ታስሮ ቤት እስኪቀመጥ ድረስ ሆኗል፡፡

ለተሻለ ህክምና ሲባል ባለቤቱ ወደ ውጭ ልትወስደው እንደምትችል የጎሲፕ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

Advertisements
Explore posts in the same categories: Gossips

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s


%d bloggers like this: