የኦሊምፒክ ጀግና አትሌት ፊጣ ባይሳ ታሰረ

የኦሊምፒክ የነሃስ ሜዳሊያ አሸናፊና የበርካታ ውድድሮች አሸናፊ አትሌት ፊጣ ባይሳ ባሳለፍነው ሳምንት ጥቅምት 2/2002 በቁጥጥር ስር መዋሉን በ98.1 ኤፍ ኤም የሚተላለፈው የኢትዮፒካ ሊንክ ፕሮግራም ዘገበ፡፡ እንደ ኢትዮፒካ ሊንክ የውስጥ አዋቂ ፕሮግራም ዘገባ መሰረት አትሌቱ በባለቤቱ በወ/ሮ ወለላ ብሩ ጉደታ እና በልጆቹ ላይ ባደረሳቸው በርካታ ጥቃቶች ተከሶ ፍ/ቤት ለመቅረብ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ፍ/ቤት ታስሮ እንዲቀርብ ትእዛዝ ቢያወጣበትም ሳይያዝ ለበርካታ ወራት በድብቅ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡

ፊጣ በፖሊስ ተይዞ ፍ/ቤት እንዲቀርብ በተወሰነበትና ከፖሊስ ተሰውሮ በቆየበት ወቅት ባለቤቱን በሽጉጥ ተኩሶ በማቁሰልም በሰበታ ፖሊስ ታስሮ በ5000 ብር ዋስ መፈታቱን የኢትዮፒካ ሊንክ ውስጥ አዋቂ ፕሮግራም የወሊሶ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጠቅሶ ዘግቦ ነበር፡፡

ፊጣ ባለቤቱ ላይ የመግደል ሙከራ አድርጎ በጥይት ያቆሰለው ባለቤቱ ሰበታ የሚገኘው ንብረቱን በህግ ለማሳገድ በተንቀሳቀሱበት ጊዜ ነው፡፡

ኢትዮፒካ ሊንክ በተደራራቢ ወንጀሎች ሲፈለግ የነበረው ፊጣ በአዲስ አበባ ፖሊስ ክትትል በቁጥጥር ስር የዋለው በአስገራሚ ሁኔታ በፌዴራል ፖሊስ ግቢ ውስጥ መሆኑን ጠቁሟል፡፡ እንደዘገባው መሰረት ፊጣ የፍ/ቤት ትእዛዝ ወጥቶበት በፖሊስ በሚፈለግበት ወቅት በፌዴራል ፖሊስ እየገባ የአሰልጣኝነት ስራውን ያከናውን ነበር የሁለት ወር ደመወዙንም በልቷል፡፡

የኢትዮፒካ ሊንክ አዘጋጆች ወሬውን ሲያቀርቡ ባይጠቅሱትም በአትሌቱ መያዝ ደስ እንዳላቸው መገመት ይቻላል ምክንያቱም ጉዳዩን በተከታታይ ሲዘግቡ በአትሌቱ ዛቻ እንደደረሰባቸው በአንድ ወቅት ገልፀው ነበር፡፡

Advertisements
Explore posts in the same categories: News

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s


%d bloggers like this: