መለስ ዜናዊ VS ቀነኒሳ በቀለ (P2)

ቀነኒሳ በቀለ በአንዳንድ ወዳጆቹ ምክር መሰረት ልክ ኃይሌ ገ/ስላሴ ሽማግሌ ሆኖ ከመንግስት ጋር በመደራደር የቅንጅት አመራሮችን ከእስር እንዳስለቀቀ ሁሉ እሱም ቴዲ አፍሮን ለማስፈታት ጠ/ሚ መለስ ዜናዊን በስልክ አነጋግሮ አልተሳካለትም፡፡ ‹ቴዲ የማይፈታ ከሆነ ዜግነቴን እቀይራለሁ› በማለት ለሰነዘረው ማስፈራሪያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጡት ምላሽ እንቅልፍ ነስቶታል… ‹ቀነኒሳ አገራችንን ያኮራህ ወደፊትም የምታኮራ ጀግና ነህ እንወድሃለን እናከብርሃለን… ይህ የህግ የበላይነት ጉዳይ ነው በዚህ ከመጣህ አይደለም ዜግነትህ ፆታህን መቀየር ትችላለህ› ነበር ያሉት፡፡

ቀነኒሳ በዚህ ተስፋ ቆርጦ መቀመጥ አልፈለገም ስለሆነም ቀጠሮ አስይዞ በአካል ጠ/ሚ ቢሮ ሄደ፡፡

ቀነኒሳ፡ ክቡር ጠ/ሚ ሽምግልና በአንዴ እንዳማይሳካ ተከታታይ ጥረት እንደሚያስፈልገው ፕ/ር ኤፍሬም ይስሃቅ መክረውኝ ነው ልምምዴን አቋርጬ የመጣሁት

መለስ፡ ትክክል ነው ይህ የድምፃዊው ጉዳይ ግን ህግ የያዘው ጉዳይ ስለሆነ በፍ/ቤት የሚያልቅ እንጂ በሽምግልና… በድርድር የሚሆን አይደለም

ቀነኒሳ፡ የቅንጅቶችም እኮ ህግ ይዞት ነበር…

መለስ፡ አዎ ግን ያ ፖለቲካዊ መፍትሄ የሚሻው ትልቅ አገራዊ ጉዳይ ነበር ይህ ግን ተራ የሰው መግደል ወንጀል ነው… በዛ ላይ ሰው ገጭቶ እንደሄደ የሚያሳይ የቪድዮ ማረጋገጫ ተገኝቷል

ቀነኒሳ፡ (በድንጋጤ) የት… መቼ?… ይህንን አልሰማሁም

መለስ፡ እንዲያውም አንድ ድምፃዊ ነው ድርጊቱን በቪድዮ ቀርፆ ያመጣልን

ቀነኒሳ፡ (አሁንም በድንጋጤ) ድርጊቱን የቀረፀው ድምፃዊ ማን ነው ክቡር ጠ/ሚ?… ያ ጠበቃ… ቴዲ ሞሲሳ ነው የሚሆነው መቼም

መለስ፡ አይደለም ይርዳው ጤናው ነው (ሳቅ)

ቀነኒሳ፡ (ሳቅ) ሰሩልኝ ጠ/ሚ

መለስ፡ በል ጨዋታ ጨዋታ ነው ወደ ቁምነገሩ ስንመለስ የድምፃዊው ጉዳይ በፍ/ቤት ነው የሚያልቀው

ቀነኒሳ፡ እባክዎትን ጠ/ሚ በለንደን ማራቶን ሁለት ወርቅ እደግማለሁ… ለእኔ ሲሉ ይፍቱት

መለስ፡ ባስደስትህ ደስ ይለኝ ነበር ነገር ግን የሚሆን አይደለም… ቴዲ አፍሮን ከመፍታት አዜብን መፍታት ይቀለኛል

ቀነኒሳ፡ (በድንጋጤ ክው ብሎ ወጣ)

Advertisements
Explore posts in the same categories: Jokes!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s


%d bloggers like this: